Thursday, June 16, 2016

በትግራይ ክልል ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የህዝብ ንብረትና ገንዘብ በመዝረፍ ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ።



   በትግራይ ክልል  ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ነጋሽ ቀበሌ የሚገኙ የስርአቱ አስተዳዳሪዎች  ከወረዳው  ሃላፊዎች ጋር በመመሻጠር የህዝብን ንብረትና ገንዘብ  ለግል ኑሯቸው በማዋል  በሙስና መዘፈቃቸውን የገለፀው መረጃው ፣ በዚህ መሰረትም ለልማት እንዲውል  በማለት ህዝብ  በግዴታ ያሰባሰበሰበው 32 ሺ ብርና ከመንግስት  የተገኘውን 12 ሽ ብር  ለተተለመለት ሳይውል ሃላፊዎቹ ለግል ጥቅማቸው እንደተከፋፈሉት   ከአከባቢው የተገኘው  መረጃ ገለፀ።
  መረጃው ጨምሮ  ብዙ ወጣቶች  እርሻ መሬት  እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም  እንኳ ምላሽ የሚሰጣቸው ስላጡ  በስራ እጥነት ሲሰቃዩ የአከባቢው  ሃላፊዎቹ ግን  እርሻ መሬት እያላቸው ደራርበው በመያዝ በሃብት ላይ ሃብት በማከማቸት ላይ መሆናቸውንና   በህዝብ ገንዘብ የተገዛውን  ተንዲኖና   ነዳጅም   ከወረዳው አስተዳዳሪዎች ጋር  ተመሻጥረው    ለግላቸው ሲጠቀሙበት የታዘበው ህዝብ ጥያቄ ቢያቀርብም  ፀረ ልማትና  የአሸባሪዎች ልኡካን ናቸው በማለት እንደሚያስፈራርዋቸው ነዋሪዎች መግለፃቸው ታወቀ።
    በተመሳሳይ   በዚሁ  በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ  የሚገኙ የትምህርት ቤት ሃላፊዎች በተሌቶን  ከህዝብ የሚሰበሰበው ገንዘብ ደርሰኝ  ወረቀት  ስለሌው ተጠፋፍተዋል ብቨማለት  ህዝቡ ምሬቱ በመግለፅ  ላይ መሆኑንና  ከ60 ሺ ብር በላይ የተገኘውን ገንዘብም  ኦዲት ሲደረግ  ደግሞ 30 ሺ ብር ብቻ ገቢ እንደሆነና  በሀዝብ  ጉልበት በነፃ የተሰራው ቢሆን     በክፍያ እንደተሰራ አስመስሎው  በማቅረብ   ገንዘብ ወጪ በማደረግ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት መረጃዎቻችን ከአከባቢው ገለፁ።  

   

No comments:

Post a Comment