Thursday, June 16, 2016

የአማራ ክልል ህዝቦች አሰከፊ የደርግን ሰርአት ለማሰወገድ በጠንካራ ብርታትና መሰዋትነት ከኢትዮጵያዊያን ወንዲሞቹ ጋር በመሆን ብአዴን በሚል የድርጅት ሰም በመደራጀት ለታገሉ ነባር ታጋዮች ለማሰመሰልና ከህዝብ እየተሰጠ ያለውን ወቀሳ ለመሸፈን ሲባል ከ25 አመት በኋላ በባህርዳር ሙሉ አለም ዳራሽ በደርጅቱ ሊቀመንበርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን እውቅና ተሰጣቸው።



  ባገኘነው መረጃ መሰረት ፣የአማራ ክልል ህዝብ አሰከፊ የደርግን ሰርአት ለማሰወገድ በጠንካራ ብረታትና መሰዋትነት ከኢትዮጵያውያን ወንደሞቹ ጋር በመሆን፣ ብአዴን በሚል የደርጅት ሰም በመደራጀት ለታገሉ ነባር ታጋዮች ለማሰመሰልና ከህዝብ እየተሰጠ ያለውን ወቀሳ ለመሸፈን ሲባል ከ25 አመት በኋላ ሁሉን ታጋዮች ያላካተተና ጥቂት ታጋዮች ብቻ  በተገኙበት ሰብሰባ ማካሂዳቸው የገለፀው የደረሰን መረጃ  አንዳንዶቹ በሰጡት አሰተያያት በአሁን ወቅት የብአዴን ነባር ታጋዮች በአሳዛኝ ሁኔታ የሰራ እድል በማጣታቸው ምክንያት በቀን  ለመለመን እየፈሩና እያፈሩ በመሆናቸው ለሌት በድብቅ በልመና ሰራ ላይ የተሰማሩ እጅግ በርካታ ነባር ታጋዮች በመኖራቸው ተሰብሰቢዎቹ  በምሬት መግለፃቸው ታወቀ።  
  በመጨረሻም የክልሉ ህዝቦች  በሁሉም አካባቢዎች  ለሰላም ፣ለልማት፣ ለዴሞክራሲ ሲሉ የታገሉ በሰውነታቸው ውስጥ የጥይት ምት ያላቸው  በአሁን ውቅት  ያለምንም ደጎማ የወደቁ መሆናቸውን  በባህርዳር በሙሉአለም አዳራሽ የተገለፀ ሲሆን ፣ለተወሰኑ ታጋዮች ብቻ እወቅና የተሰጠና በርካታ ታጋዮች በተደረገው የእውቅና አሰጣጥ ይሰጣል የሚባለው  ደጎማ የታጋዮቹ  ህይወት የሚለውጥ ካልሆነ በሰተቀር ከልመና ሰራ  እንዲማይወጡ ተሰብሳቢዎች በምሬት መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል።  

No comments:

Post a Comment