መረጃው እንደሚያመለክተው በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ አንድ ቤተሰብ
አምስት ዳቦ ብቻ እየፈረመ እንዲገዛና ከአምስት በላይ ልጆች ያሉት ቤተሰብ ቢኖርም በመመሪያው መሰረት ካልሆነ በሰተቀር ከአምስት ዳቦ በላይ መግዛት እንደማይችሉ
ተገለፀ።
በተመሳሳይ
በአማራ ክልል የሚገኝ የንግድና የኢንድስትሪ ጽሕፈት ቤት፤
በክልል የሚገኙ የዱቄት ፋብሪካና፤ ዳቦ በመሸጥ የሚተዳደሩ ነጋዴዎች በተማከለ መንገድ አከፋፍላችኃለሁ በሚል ስንካላ
ምክንያት በቁጥጥሩ ስር በማዋል፣ በጥቅም ከተሳሰሩ ነጋዴዎች ጋር በመመሻጠር
በህገወጥ ንግድ በ800 ብር ሂሳብ በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ እነኝህ ከተበላሸ አሰራርና ነፃ ለሆኑት ነጋዴዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ ኩንታል በ1200 ብር ሂሳብ እየሸጡላቸው ሲሆን የእለት ጉርሻ የሌለው ድሃ ህብረተሰብ ግን ዳቦውን በመሸጥ የሚተዳደሩት ነጋዴዎች ከአምስት
ዳቦ በላይ እንዳይሸጡ ትእዛዝ እንደተሰጣቸውና ተመዝግበው ፊርማቸው እንዲያሰቅምጡ በማስገደድ እየሸጡላቸው መሆናቸውን ታወቀ።
No comments:
Post a Comment