Monday, June 13, 2016

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአሁኑ ጊዜ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ በመጠቀማቸው ምክንያት ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጠ እንደሚገኝ ታወቀ።



      ባገኘነው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ መብራትና ንፁህ የሚጠጣ ውሃ በከተማዋ ባለመኖሩ የተነሳ የአዲስ አበባ ነዋሪ ማህብረሰብ ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጠ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
      በከተማዋ ጥራቱን ያልጠበቀ የሚጠጣ ውሃና ኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ህዝቡን ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ በመጠጣቱ በርከት ያሉትን ወገኖች በተቅማጥ ብሽታ ክፉኛ እየተሰቃዩ ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ መሆናቸው ከገለፀ በኃላ የስር አቱ ጤና ሚንስተር ግን ከሁለት በሽተኞች በስተቀር ሌላ የታመመ ሰው የለም በማለት በመሬት ላይ የሚታይ የህዝቡን ችግር ሊክደው እንደቻለ ተገለፀ።
      የአዲስ አበባ ህዝብ በአሁኑ ጊዜ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ አፍልቶ እንዳይጠቀም ደግሞ የኤሌክትሪክ እጥረት ያጋጠመ ሲሆን  አሁን ተከስቶ ያለውን የተቅማጥ በሽታ እየባሰ እንዳለ ህዝቡም በዚህ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ውስት ውድቆ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ ገልፆዋል።

No comments:

Post a Comment