Monday, June 13, 2016

በስርአቱ ተሻሽሎ ወጣ የተባለው የግብር ገቢ አዋጅ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት የማያረጋግጥ እንደሆነ ታወቀ።



የግብር ገቢ መሻሻያ ተብሎ የወጣ አዋጅ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የማያደርግ ነው  ተብሎ ሲገለፅ የቆየ ሲሆን ።የኢኮኖሚና የገንዘብ  አስተባባሪ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ የግብር ገቢ አዋጅ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት  የማያደርግ እንደሆነ ተገለፀ፣ ይህ ለህዝቡ ይፋ የተደረገው አዋጅ በህብረተሰቡ ሰፊ  የመነጋገሪያ ጉዳይ በመሆኑና በተጨማሪም  የንግድ ስርአቱን እንዳይናጋ ከባድ ስጋት ፈጥሮ እንዳለ ለማውቅ ተችሏል።
   እስከ አሁን ድረስ ሲሰራበት  የቆየው የግብር ገቢ አዋጅ ተሻሻለ በተባለበት ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቅም እንዳልሆነ የሚታወቅ ሲሆን። አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች የግብር ገቢ መቀነስ ትርፉ የገበያን ዋጋ ከፍ እንሚያደርግና አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል በማለት ከባድ ስጋት ውስጥ ወድቆ እንዳለ ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።
የኢኮኖሚና የገንዘብ  አስተባባሪ የልማት ሚኒስቴር አቶ አብዱል አዚዝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት  ለሚቀጥለው አመት የተመደበው በጀት 274.3 ቢልዬን ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት በ50 ቢልዬን ከፍ ያለ እንደሆነና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የማያደርግ መሆኑን አንዳንድ የህብረተሰብ  ክፍሎች በመግለፅ ላይ እንዳሉ ለማውቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment