Monday, June 13, 2016

በኦሮምያ ክልል በጅማ ዞን ዴዳ ወረዳ ሞሌ በተባለ ቀበሌ በኢህአዴግ ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ተቃውሞ በህዝቡ እንደተነሳ ተገለፀ ።



በደረሰን መረጃ መሰረት  በኦሮምያ ክልል በጅማ ዞን በዴዳ ወረዳ   ሞሌ በተባለ ቀበሌ በኢህአዴግ ስርዓት ላይ  ያነጣጠረ ተቃውሞ  በህዝቡ እንደተነሳ የገለፀው መረጃው በተጨማሪ ህዝቡ በዚህ ተቃውሞ የመብት ጥያቄዎች በማንሳት ቁጣውን በመግለፅ እያሰማቸው ከነበሩ  መፈክሮች ውስጥ የመልካም አሰተዳደር ችግር አለብን  የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በሮመዳን ፆም መካሄድ የለበትም መንግስት ይህን የፈተና ጊዜ በአሰቸኳይ መቀየሩን ያሳውቀን የማይቀይር ከሆነ ግን ተቃውሞው ቀጣይ ነው ።እንዲሁም መብታችን  እንዲከበር ጥሪ እናደርጋለን መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቋርጥ የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች በመያዝ ተቃውሟቸውን እያሰሙ እንደነበር የደረሰን መረጃ ጨምሮ አሰረድቷል።

No comments:

Post a Comment