Tuesday, June 7, 2016

በታላቅ ችግር ላይ የሚገኘው የሃራማያ ዩኒቨርስቲ ወደ ትምህርታቸው ያልተመለሱ የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ እንደተወሰነ ተገለፀ።



    በሃራማያ ዩኒቨርስቲ  የሚማሩ የአንድ አመት የኢንጂነሪግ  ተማሪዎች /ስቴንሽን ካምፓስ)  የማሰጠንቀቅያ  ጥሪ እንደተላልፈላቸው የገለፀው መረጃው  ዩኒቨርስቲው  የሰጠው መግለጫ ተማሪዎቹ ትምህርታቸው አቁመው መቆየታቸው በማስተዋስ  ወደ ክፍላችሁ ግቡ ብለን  ስንጠይቃቸው  አንመለስም ብለዋል በሚል ሰንካላ ምክንያት ተማሪዎቹ ከግቢው  እንዲወጡ መወሰኑ ተገለፀ።

  ዩኒቨርስቲ ሃራማያ በዚህ በቅርብ ግዜ ኣስቸኳይ  ስብሰባ እንዳካሄደና የዩኒቨርስቲው ሴኔትም  በበኩሉ ከትምህርት ገበታችሁ ለአንድ ሳምንት ኣቋርጣችሁ የቆያቹህ ተማሪዎች  ከዩኒቨርስቲው ግቢ ወጥታችሁ ሂዱ የሚል ውሳኔ  ማስተላለፉ መረጃው አስረድተዋል።

     መረጃው ጨምሮ  የዩኒቨርስቲው ደንብና የሴኔቱ ውሳኔ  ያለማክበራችሁ፤ የተሰጣችሁ እድልም ልትጠቀሙበት ስላልቻላችሁ፤  የዩኒቨርስቲ ሴኔት  ባስተላልፈው ውሳኔ መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ ከአሁንዋ ሰአት ጀምራችሁ  ማስታወቅያችሁ፤ የመመገብያ ካርዳችሁንና ሌላው የዩኒቨርስቲው ንብረት  ኣስረክባችሁ ውጡ የሚል ማስታወቅያ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ እንደተለጠፈ ተገለፀ።

No comments:

Post a Comment