መረጃው እንዳመለከተው በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል እየተሰራ ያለው የአባይ ግደብ
ውሃ ይደርስበታል በሚል ምክንያት ነዋሪዎች ከአካባቢው ወደ ሌላ ቦታ ተወሰደው እንዲቀመጡ ቢደረግም፣- ይሰጣችኋል የተባለው ካሳ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ነበሩበት ቦታ በራሳቸው ተመልሰው እየሰፈሩ እንዳሉ
መረጃው አስረደቷዋል።
በዚህ ጉዳዩ
ላይ ራሱን የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት ብሎ በሚጠራው ቡድን በግንቦት
25/2008 ዓ/ም ለምንድን ነው እስከ አሁን ደረሰ ይሰጣችሁል የተባለው
ካሳ ያልተሰጣቸው፣ የሚል ጥያቄ ተነሰቶ እንደነበረ ከገለፁ በኃላ-ለዚህ
ጥያቂ መልስ የሰጡት ሚኒሰተር ዴታ አቶ ካይድኪ ገዘሀኝ ይሰጣችኋል የተባለው ካሳ እንደዘገየ ገልፀው፣- በዚህ በቅርብ ቀን ይህ ጉዳይ በቦርድ ተገምግሞ በኢትዮጵያ የኤሊክትሪክ ሃይል ይህ
ካሳ ሊሰጣችሁ ነው የሚል መልስ ቢሰጡም እንኳን፣ ቀልጣፋና ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንደማይሰጡ የተለያዩ ወገኖች
በመግለፅ ላይ እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አሰረድቷዋል።
No comments:
Post a Comment