Thursday, June 30, 2016

በኢትዮጵያ በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርተው የሚገኙ ወገኖች በትግራይ ክልል ትልቅ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።



ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ በጋዜጠኝነት ሙያ ተመርቀው በተለያዩ ሚዲያዎች ተቀጥረው የሚያገለግሉ ጋዜጠኞች ከሁሉም የአገራችን ክልሎች በተለይ በትግራይ ትልቅ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው በሙያው ተሰማርተው የሚገኙ ወገኖች አስረድተዋል።

   እነዚህ ወገኖች እንዳስረዱት እንደሚዲያ ሰራተኛ መጠን ወደ ትግራይ በምንቀሳቀስበት ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ ብለን ከገለጽን፣ በስርዓቱ ካድሬዎች ማስፈራራትና ዛቻ ይደርስብናል፣ በስራችን ላይ ደግሞ እንቅፋት ይበዛብናል በማለት ሲገልፁ፣ በተጨማሪም በትግራይ ክልል የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሩ ጋዜጠኞች ያስረዳሉ።



No comments:

Post a Comment