Thursday, June 30, 2016

ኢትዮ-ቴሌኮም በስርአቱ ኢ-ዴሞክራስያዊ አስተዳደርና ማጭበርበር ምክንያት ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው ታወቀ።




   በኢህአዴግ ስርአት ቁጥጥር ስር የሚተዳደረው ኢትዮ ቴሌኮም በማጭበርበር ምክንያት ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት የጠቆመው መረጃው፣ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ አማራጭ የሚያገኙበት መንገድ ባለመኖሩ ተገደው በስርአቱ ስር በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በመሆን አብዛኞቹ የስልክ አገልግሎት፣ ኢንተርኔት፣ፋክስ በየቀኑ እየተቆራረጠ በመሆኑ ለህዝብ አስፈላጊ አገልግሎት የማይሰጥ ድርጅት እንደሆነ በመግለፅ፣ በዚህ መሰረት ደግሞ ህዝብ ፈጣን አገልግሎት ሳያገኝ ገንዘቡን እየተመዘመዘ በመሆኑ እንዲስተካከልለት በተደጋጋሚ ጥያቄዉን ቢያቅርብም እስካሁን ድረስ  መፍትሔ ሊያገኝ እንዳልቻለና ኢትዮጵያ በቴሌኮም ቴክኖሎጂ ከአለም ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ አገሮችም መጨረሻ እንደምትጠቀስ መረጃው ጨምሮ አስታዉቋል።
   አስተያየት ሰጭዎች ስርአቱ የቴሌኮም አገልግሎትን ችግር ሊፍታው ያልቻለበት ምክንያት ሲገልፁ፣ በስልክና ኢንተርኔት የሚደረጉ የመረጃ መለዋወጥ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ወጭ በማድረግና የመረጃ መረብ በመዘርጋት የሚተላለፉ መልእክቶች እየጠለፈ ሰላማዊ ዜጎች በስዉርና በገሃድ እየወሰደ ወደ እስርቤትና ሞት የሚሰራበት ድርጅት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። 
   ከከፍተኛ አመራሮች እየተመሻጠሩ በማጭበርበር ተግባር ተሰማርተው የህዝብን ገንዘብ እያባከኑ ረጅም ጊዜ ያሰቆጠሩ አካላት የስርአቱ ተላላኪዎች እንደሆኑ  የገለፀው መረጃው፣ የዚህ ተግባር በሰፊው የሚታይባቸው አከባቢዎች ደግሞ አዲስ አበባ ፣ ጅግጅጋ፣ሃረርና ድሬዳዋ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰም ለማወቅ ተችሏል፣

No comments:

Post a Comment