Thursday, June 16, 2016

በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን የማይ ካድራ ከተማ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ቆጣሪና ትራንስፎርመር ችግር ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ እንደሚገኙ ታወቀ።



መረጃው እንዳስረዳው በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን ማይ ካድራ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በአኤሌክትሪክ ቆጣሪና ትራንስፎርመር እጠረት  ከምንጋለጥ ቡዙ አመታት አስቆጥረናል ካሉ በኃላ በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ብዛት ያለው የከተማዋን ነዋሪ ከነበረው የህዝብ ብዛት በከፋ መልኩ እየጨመረ በመሆኑ ችግሩን ወደ በከፋ መልኩ ደርሶዋል በማለት ስማቸው ለመግለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
      የማይ ካድራ ከተማ ነዋሪዎች ቀደም ሲል አንድ ቆጣሪ ለመግዛት ከ1500 ብር እስከ 2000 ብር ዋጋው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ እስከ 10ሺ ብር ደርሶዋል በማለት ጨምረው ሲገልፁ ደግሞ ቆጣሪውን ለማግኘት ሲባል ጉቦ ካልሰጠህ በስተቀር ፍትሃዊነት በተሞላው መልኩ ለማግኘት የማይታሰብ ነው ለዚህ ደግሞ በቅርብ አቤቱታችን ሰምቶ መልስ የሚሰጥ የመንገስት አካል አጥተናል በማለት የከተማው ህዝብ እየገለፀ ይገኛል።
    በመጨረሻም ማይ ካድራ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎሁ ቤቶች በቆርቆሮና ግድግዳ የተሰሩ በመሆናቸው የተነሳ በትራንስፎርመር እጥረቱ ምክንያት ከልክ በላይ ህዝቡ በአንድ ትራንስፎርመር ብቻ ስለሚጠቀም ከብዛት የተነሳም በከተማዋ የእሳት ቃጠሎ እንዳይነሳ ህዝቡ በስጋት ላይ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment