Wednesday, August 24, 2016

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ ጥር ወር ድረስ የአሜሪካን ዜጎች በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ጉብኝት ማሰጠንቀቂ እንደዘረጋ ታወቀ።



መግለጫው እንደሚያስረዳው፤ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመንግሰት ላይ ተቃውሞ እየተከሰተ በመሆኑ በተለይም ደግሞ በአንዳንድ የመንግሰት ታጣቂዎችና ሰልፈኞቹ ከባድ የሆነ ግጭትና ሁከት እንዳስከተለ በመግለፅ የቴሌፎንና የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠና እየተዘጋ ስለሆነ የአሜሪካ ኢምባሲ ከዜጎቹ ጋር ለመገናኘት አሰቸጋሪ እንደሆነበት  በመግለጫው አሰረድቷል።
   ከህዳር ወር የጀመረው ፀረ መንግሰት ተቃውሞ ከቀን ወደ ቀን ያለምንም እረፍት ተጠናክሮ እየቀጠለ በመሆኑ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች፣ በተቃዋሚዎችና በመንግስት ሃይሎች መካከል ከባድ ግጭትና ግድያ እንደተፈጠረ በመግለፅ፣ ይህ ተቃውሞ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ሌሎች ከተሞች እየተሰፋፋ በመሆኑ፣ የአሜሪካ ዜጎች ትኩረት አደርገው ከሰልፎችና ትላልቅ ሰብሰባዎች ከሚካሄዱባቸው የኢትዮጳያ ቦታዎች እንዲርቁ  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ለዜጎቹ ማሰጠንቀቂያ እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል።



No comments:

Post a Comment