Wednesday, August 24, 2016

በዚህ ሳምንት በሃገራችን ኢትዮጵያ በአተት በሽታ የተጠቁት የታማሚ ቁጥር የተያዙ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ቸምሪ ኣንደሚገኝ ታወቀ።



በተገኘው መረጃ መሰረት- ቀደም ሲል የተቅማጥ በሽታ የተያዙት በ አኦሮምያና በሱማሌ ክልሎች በስፋት እንደተዛመተ የሚታወቅ ሲሆን። በዚህ ሳምንት ደግሞ በአማራና በትግራይ ክልሎች በተለይ ደግሞ በመቐለ ከተማና በአማራ ክልል ደግሞ በባህርዳር ከተማ በሽታው እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተገለፀ።
       እንደ መረጃው አገላለፅ።- በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል ከ450 የሚያህሉ ሰዎች በተቅማጥ በሽታ ኣንደተያዙ ከገለፀ በኋላ። ባጠቃላይ ካለፈው አመት ነሃሴ ወር ጀምሮ በአኦሮምያ፤ ሱማሌና ደቡብ ክልሎች ብቻ 19 ሰዎች በተቅማጥ በሽታ ምክንያት እንደሞቱና 2000 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ እንደታመሙ የአባበሩት አንግስታት የሰብ አዊ መብት አስተባባሪ ፅህፈት ቤት ካወጣው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል።
         በተጨማሪም።- በአዲስ አበባ ህዝብ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃን በመጠቀሙ ምክንያት ከሰኔ ወር 2008ዓ/ም ጀምሮ በሽታውን እየተስፋፋ እንደመጣ የሚታወቅ ሲሆን። በዚህ ሳምንት ግን በከፈተኛ ደረጃ በርከት ወዳሉትን አካባቢዎች እንደተስፋፋና በአዲስ አበባ ቦሌ ክፈለ ከተማ፤ አቃቂ፤ የካ፤ ኮፌ እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፈለ ከተማ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ መረጃ አክሎ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment