Wednesday, September 21, 2016

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከነሃሴ 28 20008ዓ/ም እስከ ጵጉሜ 4 2008ዓ/ም ታሪካዊና 2ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በማሳለጥ በድል እንዳጠናቀቀ የትህዴን ፖለቲካዊ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።



የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በ2007ዓም መጨረሻ ካጋጠመው የድርጅቱ መሪ የነበረው ሞላ አስገዶም ወደ ጠላት የመፈርጠጥ ምክንያት ተነስቶ ለአንድ አመት ያህል በሰራዊቱ ውስጥ ሰፊ የፖለቲካ ስራ ሲሰራ ቆይቶ እንዲሁም የማታገያ ፕሮግራሙ ሲገመግምና ሳያጠራ በመቆየት ከነሃሴ 28 2008ዓ/ም ጀምሮ ለሰባት ቀናት ያህል መድረክ በማሳለጥ ሁለተኛውና ታሪካዊ ጉባኤውን በድል አጠናቅቀዋል።
ጠላት በፈበረከው መርዛማ ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተወሰኑ በሽተኖችና የተዳከሙ ታጋዮች ብቻ ይዞ ነው የቀረው የሚል የተስፋ መቁረጥ ሲያካሂደው የነበረው የከሰረ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ዴሞራሲያዊ ንቅናቄ ጠንካራነት የማያውቁ የተወሰኑ ወገኖች ሊያደናግር ሞክሮ እንደነበረ  የሚታወስ ነው ያለው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ፅህፈት ቤት። የትህዴን ከፍተኛ አመራሮችና ታጋዩ የጠላት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ዳባ ብለው ውስጣዊ ሁኔታቸው በመፈተሽ ከቆዩ በኋላ ሁለተኛና ታሪካዊ ጉባኢያቸውን በድል  ለማተናቀቅ በቅተዋል ሲል አስታውቋል።
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን በዚህ በሁለተኛው ድርጅታዊ ጉባኤውን ድርጅቱን ሊመሩ ይችላሉና ድርጅቱን ወደ ላቀ ደረጃ ያሻጋግራሉ ያላቸውን ለሁለቱም ፆታዎች ማእከል ያደረገ ህብረ ብሄራዊ አመራር የታየበትና ተሳትፎ ያለውን በታሪኩ ዴሞክራሲ የሰፈነበት አዲስ መዝገብ እንዲያስፍር ያስቻለው መሪዎችሁን በዴምክክራሲ መንገድ እንዲመርጥ አስችሎታል።
እነዚህ በታጋዩ የተወከሉ የጉባኤው ተሳታፊ ታጋዮችም በሁለተኛውና ታሪካዊ ጉባኤ በመሳተፍ ለሰባት ቀናት ያህል የጨረሰው ሰፊና ጥልቀት ያለውን ክርር የታከለበት ድርጅቱን ያሰሩታል ያሏቸውን በረከት ያሉት አስተያየቶችና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጳጉሚ 4 2008ዓ/ም ሁለተኛውና ታሪካዊ ጉባኤውን በይፋ አጠናቅቀዋል።
በጉባኤው የተሳተፍ ታዳሚና ተሳታፉ የሆኑት እንግዶች በበኩላቸው ጠላት ጨረሰው ይጠፋሉ በሚልበት ወቅት  እንደዚህ ብላችሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጠንክራችሁና አንድነታችሁ በመጠበቅ ሌሎች አገሮች እንዃ ሊደፍሩት ያልቻሉት የዴሞክራሲ ድባብ በማምጣት   ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የምርጫ መድረክ መድፈራችሁ መጭው የዴሞክራሲያዊ ማንነታችሁና ድርጅታችሁ የሚያጎላ መሆኑ ተረድተናል ሲሉ  ገልፀዋል።         

No comments:

Post a Comment