Monday, October 31, 2016

በዚህ ሳምንት ከተለያዩ የአገራችን አከባቢዎች የኢህአዴግ ስርአት በመቃወም በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል እንደተቀላቀሉ ወኪላችን ከማሰልጠኛ ማእከሉ ከላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



የትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል በላከልን መረጃ መሰረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተለያዩ የአገራችን አከባቢዎች በቁጥር በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግሉ ጎራ እየተቀላቀሉ እንዳሉ በመግለፅ የዚህን ቅጥያ ደግሞ በዚህ ሳምንት በአገራችን ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ቀዉስ ለመፍታት ለስርአቱ በመቃወም ዋናዉ መፍትሔው የትጥቅ ትግል መሆኑን በማመን ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ መቀላቀላቸዉን ገለፁ።
    ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ ከተቀላቀሉት ወጣቶች የተወሰኑት ለመጥቀስ ያህል።
1.መምህር ፅጋቡ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉለመኸዳ ወረዳ ቅልዓት ቀበሌ በመቀሌ ዩንቨርስቲ በመምህርነት ሞያ እየሰራ የነበረ።
2 በያን ተክሉ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ሆያ ቀበሌ
3 ተስፋይ ሓጎስና ሳሙኤል ግደይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ዓገረለኹማ ቀበሌ፣
4. ፀሃየ አርአያ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉለመኸዳ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ እንዲሁም ምሕረት አለማ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ወርዓትለ ቀበሌ የሚገኝዋቸው እንደሆኑ ገጿል።

ወጣቶቹ ወደ ትህዴን ድርጅት በመቀላቀል እንዲታገሉ የወሰኑበት ምክምያት ሲገልፁ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ገዢው ስርአት በፈጠረው መጥፎ አስተዳደር ምክናይት ከሌሎች ቢሄሮች እንዲነጠል እየተደረገ በመሆኑና በአጠቃላይ ደግሞ በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እየወረደ ለሚገኝ እልቂት ለማስወገድ ትግል እንደመረጡ ገልፀዋል።
እነዚህ ወጣቶች ኣስከትለው በተለይ ደግሞ መምህር ፅጋቡ አብረሃ በመቀሌ ዩንቨርስቲ ሌክቸረር ሆኖ እየሰራ በነበረበት ወቅት ሲመለከተው የነበረ የትምህርት ጥራት ችግር ሲገልፅ፣ የአገራችን የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የሚያስፈልግ ብቃት ጨብጠው እንደማይወጡና በአጠቃላይ በአገራችን ያለ የትምህርት ጥራት የተዳከመ መሆኑን አስረድቷል።


No comments:

Post a Comment