Thursday, November 17, 2016

የኢትዮጵያ ህዝብ የኢንተርኔት አገልግሎትና ሶሻል ሚዲያ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት እስከወዲያኛው ሊዘጋው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



   የኢንተርኔት አገልግሎቶችና ሶሻል ሚዲያዎች ግብአተ መሬት እንደገቡና እስከወዲያኛው ተዘግተው እንደሚቆዩ ከውስጥ አወቆች ጥቆማ መረዳት ተችሏል
    ወያኔ የቻይናን የሶሻል ሚዲያ ማለትም የፌስቡክ፣ የኢንስታግራም፣ የቫይበር፣ የኋትስአፕና የመሳሰሉትን ልምድ ሥራ ላይ አውሎታል፡፡ በዚህ የኢንተርኔት አፈና በደምሳሳው ስሌት ኢትዮጵያ የምታገኘው የነበረውን ከሰማንያ ሚሊዮን ብር በላይ ማጣትዋ ታውቋል
   በተመሳሳይ ስርአቱ በሳተይላት የሚሰራጩ የተቃዋሚ የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ማየት ክልክል መሆኑንና በሳተላይት የሬድዮ ስርጭቶችን ማድመጥ ቢከለክልም ሕዝቡን ግን ከማየትና ከማድመጥ ማስቆም አለመቻሉን በመረዳት በየቤቱ እየዞረ ከሳተላይት መቀበያ የሆነውን አል. ኤን.ቢ. የሚባለውን በተወሰኑ ሰፈሮች ከሳተላይት መቀበያ ሰሀኖች ላይ በፌደራል ፖሊሶች አማካኝነት እያስነቀለ መሰብሰቡ የሚታወስ ሆኖ ይህ ድርጊት ግን በቃሬዛ ላይ መንፈራገጥ ከመሆን የማይዘል መሆኑን ብዙ ወገኖች ያስረዳሉ

No comments:

Post a Comment