Thursday, November 17, 2016

በኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ. ስርጭት በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን በበሽታው ላይ ጥናት ያካሄዱ ተመራማሪዎቹ አስታወቁ።



ሰሞኑን ይፋ ከተደረጉ ጥናቶች መገንዘብ የተቻለው በትላልቅ ከተሞችና በመለስተኛ ከተሞች በተደረጉ ጥናቶች በሽታው ወጣቶችንና ታዳጊ ወጣቶችን በወረርሽኝ ዓይነት ሁኔታ እያጠቃ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል
    በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በናዝሬት፣ በጂማ፣ በሀዋሳ፣ በዲላ፣ በአርባ ምንጭ ወዘተ. በበሽታው የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ለረጅም አመታት በበሽታው ላይ ጥናት ያካሄዱ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ
    ለበሽታው መስፋፋት ዋነኛ ሰበቦች መሆናቸው የተጠቀሱት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ለወጣቶች ትኩረት አለመስጠቱንና  የተለያዩ አደንዛዥ እጾች በስፋት በወጣቶች አካባቢ እንዲስፋፉ በማድረጉ አንዱና ዋነኛው ሲሆን  ከዚህ ጋር ተያይዞም  ልቅ የሆኑ የዳንኪራ ቤቶች እንደ አሸን መፍላታቸው መሆኑ በቀረቡት ጥናቶች ላይ ተወስቷል
    ሌላው የወያኔ ባለስልጣናት ከአንድ የህንድ ኩባንያ ጋር በመመሳጠር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቧቸው ቀዳዳ ኮንዶሞችም የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው
    ወያኔ የወጣቱን ስነልቡና ለማሽመድመድ ወጣቱን ለተለያዩ ሱሶች ተገዢ እንዲሆን በስልት እየሰራ መሆኑን በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያስረዳሉ


No comments:

Post a Comment