በመረጃው
መሰረት የጎንደር ዩኒቨርስቲ የህክምና ዲፓርትመንት ተማሪዎችስራ
የማግኘት እድላችን በመናመኑ ምክንያት ሌላ ዲፓርትመንት
ይቀየርልን ስላሉ ብቻ የአስቸኳይ የግዜ ኣዋጅ መምርያ
ጥሳችህዋል በሚል ስንካል ምክንያት በህዳር 19 ቀን
2009 ዓ/ም 102 ተማሪዎች በፈደራል ፖሊስ ታፍነው ወደ ኣልታወቀ ስፍራ እንደተወሰዱና እስከ አሁንም
የት እንደገቡ ኣልታውቀም በማለት ከተማሪዎቹ በኣማርኛ ለሚሰራጨው
ሬድዮ ኣሜሪካ ከሰጡት ቃል ለማወቅ ተችለዋል።፣
የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪ በበኩላቸው
የተማሪዎቹ ተገን ከመሆንና ጥያቄዎቻችውን ስምተው ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ፈንታ ከስርኣቱ ፀጥታ ሃይሎች በመተባበር
ተማሪዎችን በሃይል ኣፍነው እንዲወሰዱ አድርገዋል
ያሉት ተማሪዎቹ በዚህ የተነሳ ደግሞ በጎንደር ከተማ
በተለይ ደግሞ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ውጥረት ነግሰዋል በማለት ተማሪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment