Wednesday, November 30, 2016

በአክሱም ከተማ የሚጠጣ ንፁህ ውሃና የመብራት ችግር ስለ አጋጠመ ነዋሪዎቹ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ታወቀ።



በመረጃው መሰረት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ያጋጠማቸው የውሃና የመብራት ችግር እንዲፈታላቸው ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም እስከ እሁን ድረስ ችግራቸው አይቶ መፍትሄ የሚስጥ ኣካል እንደሌለና በተለይ የድርጅቶች ባለቤት የሆኑ ሃብታሞች በመብራት እጥረት ምክንያት በስራቸው ትልቅ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።
የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ነጋ ጠባ ግምገማና ተሃድሶ በማካሄድ በህዝብ ላይ ሲታዩ የቆዩትን መሰረታዊ ችግሮች ለማሰወገድ  ኣስቸኳይ መፍትሄ እናደርግለታለን ቢሉም እስከ ኣሁን ድረስ  የተደረገ መፍትሄ ኣለመኖሩን የገለፁት ነዋሪዎቹ፣  በአክሱም ከተማ  ያለው የውሃና የመብራት እጥረት ኣሁን የተከሰተ ሳይሆን ብዙ ኣመታት ያስቆጠረ ችግር መሆኑ ነዋሪዎቹ በምሬት ገለፁ።       
ይህ እንዲህ እንዳለ ሌሎች ከተሞችን ትተን ትላልቅ ከተሞች የሚባሉትም መቀለ፤ ሽረ ሑመራ፤ ዓዲ ግራትና ማይጨውም የውሃና የኤሌክትሪክ ችግር መኖሩን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችን  ይታወሳል።
  

No comments:

Post a Comment