Friday, December 9, 2016

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገዥው የህወሃት ኢህ አዴግ አገዛዝ በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመዉን የሰባዊ መብት ረገጣና አገር እና ህዝብን የማጥፋት ወንጀል መቃወማቸውን ተገለፀ።



በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የህወሃት አገዛዝ በመቃወም ባደርጉት ስብሰባ ከተነሱት ነጥቦች መካከል” የሀወሃት መንግስት    ዲሞክራሲያዊ መብታችንን ከመግፈፍ ባለፈ ሁኔታ በህይወታችን ላይ ሊያደርስ የሚችለዉን አደጋ ሸሽተን በተጠለልንበት ደቡብ አፍሪካ ድረስ ተከትሎን በመምጣት የሚፈጽማቸዉን የሞራል ጉዳት፣ የመኖር ህልዉና ጥቃት፣ የዛቻና የማስፈራራት ተግባራቶችን ባጋለጠ መልኩ ለሁለት ሰአታት  የዘለቀ ውይይት  መደርጉን  መረጃው ገልፀዋል።
መረጃው ጨምሮ በስብሰባው የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ ጄኔራል ጋር ተገኝተው ባደረጉት ንግግር  የኢትዮጵያ ገዢ ስርአት  እየሄደበት ያለዉ መንገድ እጅግ አሳዛኝና የማያዋጣ ነዉ በማለት ያስቀመጡ ሲሆን በዲፕሎማቲክ የደህንነትና የፖሊስ መረጃ ዉስጥ የሚሰሩ አንድ ኮረነ አክለዉ “በአስገራሚ ሁኔታ የራሱን ዜጎች በሆነዉ ባልሆነዉ በመክሰስ መወንጀል  የዘቀጠ መንግስታዊ ስህተት በዚህ ክ/ዘመን መመልክት የሚያሳዝን ነዉ በማለት ገለጸዋል። 


No comments:

Post a Comment