Friday, December 9, 2016

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲዘጋ በመደረጉ በመንግስት ላይ የዘጠን ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስመዝገቡን አንድ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው አለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ።



በአገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት11 ወራቶች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሲባል መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲዘጋ  በማድረጉ የዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ወይም የ200 ሚሊዮን ብር አካባቢ ኪሳራ ማስመዝገቡን አንድ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ዘ-ብሩኪንግስ ኢንስቲቲዩቱ አለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ።
በኢትዮጵያና በሌሎች 19 ሃገራት ላይ ጥናትን ያካሄደው  ይህ አለም አቀፍ ተቋም ።ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር በሚል  ምክንያት አገልግሎቱ ይፋዊ በሆነ መንገድ ከጥቂት ወራቶች በፊት ዝግ የተደረገ ሲሆን፣ እርምጃው በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ።
በአዲስ አበባና የክልል ከተሞች የሚገኙ በርካታ ሆቴሎች እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ በስራቸው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ሲገልጹ ቆይተዋል።

No comments:

Post a Comment