በመረጃው መሰረት ባለፈው ሳምንት ከአውሮፓ አባላት ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክርን ያካሄዱት ዶ/ር መረራ ጉዲናን ከጉብኝታቸው መልስ በኢህኣዴግ ስርኣት በቁጥጥር ስር መዋላቸን የሚታወቅ ሁኖ በዚህ የተነሳ የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለእስር የተዳረጉበት ምክንያት ግልፅ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ።
ባለፈው
አመት በኦሮምያ ክልል ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የአውሮፓ ፓርላማ አስቸኳይ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረቡንና፣ የዶ/ር መረራ ጉዲናን
በመንግስት ለእስር መዳረግ ግልፅ እንዲደረግና የኢህአዴግ ስርአት በአውሮፓ ፓርላማ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደረግ ጥሪ
ማቅረቡም ታውቋል።
No comments:
Post a Comment