Friday, December 23, 2016

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካ ግቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው ለልማት ተብሎ የፈረሰባቸው ነዋሪዎች መንግስት ተለዋጭ ቦታ ለመስጠት የነበረውን ቃል አላከበረም በማለት ቅሬታቸው ማቅረባቸው ታወቀ።



 በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካ ግቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው ለልማት ተብሎ የፈረሰባቸው ነዋሪዎች መንግስት ተለዋጭ ቦታ ለመስጠት የነበረውን ቃል አላከበረም በማለት  ቅሬታቸው ማቅረባቸውና ነዋሪዎች ህጋዊ ይዞታ እያላቸው ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ለረጅም ጊዜ መቆየታቸውንና ለማህበራዊ ችግሮች ተጋልጠው እንደሚገኙ  አስታውቀዋል።
 መረጃው ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩት ነዋሪዎች የከተማው አስተዳደር ህጋዊ ምላሽ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ምክንያት ልጆቻቸው መደበኛ ትምህርታቸው መከታተል እንዳልቻሉና በላፍቶ ክፍለ ከተማ ህገወጥ የተባሉ ይዞታዎችን ለማፈረስ የተካሄደ ዘመቻ ተቃውሞን አስነስቶ ለሶስት የክፍለ ከተማው ሃላፊዎችና የጸጥታ አባላት ሞት ምክንያት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደ ዕርምጃ ደግሞ ከ10 ለሚበልጡ ሰዎች ሞት መንስዔ መሆኑ ዘግቧል።



No comments:

Post a Comment