Saturday, January 21, 2017

በትግራይ ክልል ክልተ አዉላዕሎ ወረዳ የሚገኙ የኣጉላዕ ከተማ ነዋሪዎች በወሃና የመብራት እጥረት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገለጿል።



ባገኘነው መረጃ መሰረት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣዉላዕሎ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች የኣጉላዕ ከተማ ህዝብ ለንፁህ ወሃና መብራት ችግር ተጋልጦ እንደሚገኝና የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች ደግሞ ለዚህ ችግር እያወቁ እንዳላወቁ ላጋጠመው ችግር መፍትሄ ልያድርጉለት እንዳልቻሉ ታወቀ።

በኣጉላዕ ከተማ መብራት የለም ብቻ ሳይሆን የትራንስፎርመር ችግርም እንዳለ እንዲሁም በከተማዋ ተተክለው የሚገኙ ፓሎዎች ቢሆኑም ያረጁ በመሆናቸው ወደ ቤት እየወደቁ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ  እንደሚገኙ የኣጉላዕ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።

ነዋሪዎቹ አስከትለው በሚጠጣ ንፁ ወሃ በኩልም እንስሶች በሚጠጡበት ኩሬዎችና የተጠራቀመ ወሃ መጠጣት በመቻላቸው ለተለያዩ ወሃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸው ወገኖቹ ከሰጡት መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
















No comments:

Post a Comment