Saturday, January 21, 2017

ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከሃገራችን ጠቅልሎ ሊጠፋ የሚችል በህወሓት ኢህኣዴግ የሚመራ መንግስት ከስልጣኑ ጠቅልሎ ሲወገድ ብቻ መሆኑ ተገለፀ።



 ባገኘነው መረጃ መሰረት በአገራችን ኢትዮጵያ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ጠቅልሎ መጥፋት የሚችል በኣገራችን የህዝብን አደራ ለጎን ትቶ የአገርና ህዝብ ሃብት በመዝመት ተግባር ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ የወያኔ ኢህኣዴግ ስርአት ከስልጣኑ ሲወገድ እንጂ በይስሙላ ሙስናን መጥፋት በሚል ተሃድሶ እንዳልሆነ የተለያዩ ወገኖች እየገለፁ እንዳሉ ታዉቀዋል።

በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የሚመጣ ብድርና ከተለያዩ በጎ ኣድራጊዎች የሚሰጥ እርዳታ ለባለስልጣናት ጥቅም እየዋለ መሆኑ የገለፁት ወገኖቹ፣ ይህ አሁን ሙስናን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ህዝብ ብስብሰባዎች በመጥመድ እያካሄደው የሚገኝ ግምገማና ስብሰባ በየግዜው ሲያካሂደው የቖየ የመደናገር ተግባሩን ቅጥያ መሆኑ ገለፁ።

በተጨመሪም ይህ በከፍተኛ የስርኣቱ ሃላፋዎች በብድርና እርዳታ ወደ ኣገራችን የሚገባ በቢልየኖች ዶላር የሚገመት ገንዘብ በጥቂት የመንግስት ባለስልጣናት እጅ መዋል በመቻሉ ለአገራችንና ለህዝባችን ወደ ድህነት ጓዳና የሚያስገባ እንድሁም ሃይለኛ ግርግር የሚያስከትል መሆኑን ወገኖቹ ጨምረው አስመልክቷል።


No comments:

Post a Comment