Monday, January 30, 2017

በዚህ ሳምንት በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ማሰልጠኛ ማእከል እንደተቀላቀሉ ወኪላችን ከማሰልጠኛ ማዕከል አስታወቀ።



ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ ከተቀላቀሉት የተወሰኑትን ለመጥቀስ…
ፀጋይ ገ/መድህን  ገብረፍፀ  ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፣ መረብ ለኸ ወረዳ፣ ሃፍተማርያም ቀበሌ፣ መንደር ዓዲ ሳዉል
ወልደምህረት ገ/ሚካኤል አርኣያ ከማእከላዊ ዞን፣ መረብ ለኸ ወረዳ ደብረ ሓርማዝ ቀበሌ
ተወልደ ገብረንችኤል ገብረ፣ ከማእከላዊ ዞን፣ መረብ ለኸ ወረዳ  ወዲሓዞ ቀበሌ፣ መንደር ዓዲ ጭራማ፣ የሚገኙባቸው ሲሆኑ ወደ ትህዴን መጥተው እንዲታገሉ ያስቻላቸውን ምክንያት ሲገልፁ፣ በአገራችን ያለው ስርዓት በዜጎቻችን ላይ  እየፈፀመው ያለውን አፈናና ጭቆና በመቃወም፣ እኛም እየተፈፀመ ባለው ጭቆና ሰለባ በመሆናችንና በላያችን ላይ አድሎና እንግልት ስለ ደረሰብን የዚህ አማራጭ ደግሞ ትግል መሆኑን በመረዳታችን እኛን ከመሰሉ ጭቁኖች ለህዝባቸው እና ለአገራቸው ሲሉ ከሚታገሉ ወንድሞቻችን ጋር ለመታገል መርጠናል ሲሉ ገልፀዋል።
 በተለይ ወጣት ተወልደ በኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ፍትሕ ልታገኝ ከሆነ በስልጣን ላይ ላሉት ሰዎች ከአቅምህ በላይ ጉቦ እየከፍልክ ነው ፍትህ ለማግኘት የምትችለው ሲልም ገልጿል።

No comments:

Post a Comment