Saturday, February 18, 2017

በኢሮፕ ወረዳ አካባቢ ሠፍረው ያሉት የወያኔ ወታደሮች ሲያካሂዱት የቆዩትን ወታደራዊ ስልጠና ጨርሰው፣ በከባድ የቤት ስራ ተግባር ተጠምደው እንዳሉ ታወቀ።



እየተሰራ ያለው ቤት አላማ ወታደሮች ደን እየጨፈጨፉ ከህዝብ ጋር እየተጋጩ ስላሉ፣ በአንድ አካባቢ ጠርንፎ ኤሌክትሪክ ለማስገባት ያለመ ነው የሚል መግለጫ በኃላፊዎች እየተሰጠ ቢሆንም፣ ዋና አላማው በተደጋጋሚ እየጠፉ ላሉት የስርዓቱ ወታደሮች ተከትሎ፣ አንድ ሬጅመንት በአንድ ቦታ መጠርነፍ አለበት የሚል መምሪያ ስለወረደ እየተሰሩ ያሉት ቤቶች ደግሞ ሬጅመንቷን በአንድ አካባቢ ጠርንፎ ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ ምንጮቻችን አጋልጠዋል። 
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ ወታደሮች በሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት እየፈፀሙ እንዳሉና የዚህ ውጤት ደግሞ በእንዳልጌዳ አንዲት ለጊዜው ስሟ ያልደረሰን የሁለት ልጆች እናት ሴት አስገድደው ፍላጎታቸውን ከፈፀሙ በኋላ፣ ገድለዋት  እንደሄዱ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ይህች እናት ተገድላ ድንጋይ ተጭኗት እንደተገኘች የአካባቢው ህዝብ ደግሞ ወታደሮች አስገድደው ስለደፈሯት እንዳታጋልጣቸው ሲሉ ነው ገድለዋት የሄዱ እያለ በመናገር ላይ እንዳለና፣ ወታደሮቹ ደግሞ የሴትዮዋ ሬሳ በካምፓቸው አቅራቢያ ስለተገኘ አባሎቻቸው ይህንን ተግባር እንደፈፀሙ ቢያምኑም እንኳ፣ ማን እንደሆነ ለማጋለጥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው አንድ ወታደር በጥርጣሬ ያህል ታስሮ እንዳለ ታውቋል።






No comments:

Post a Comment