Saturday, March 4, 2017

በመላው የትህዴን ሰራዊት እንዲሁም ክፍሎች የየካቲት19/ 16ኛ አመት የትህዴን የምስረታ በአል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ እንደሰነበተ ወኪሎቻችን ገለፁ።



   16አመት የድርጅታችን ትህዴን የምስረታ በአል የካቲት19 “በሞረድ ትግላችን እየተሳልን ድል እናደርጋለን” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የሰነበተ ሲሆን፣ በርከት ያሉ የትግላችን ወዳጆችና ደጋፊዎች እንዲሁም እድሜ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
   ድርጅታችን ከተሞኩሮዎቹ እየተሳለ ወደ ሙሉ ድል ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ሁለተኛ ድርጅታዊ ጉባኤው ካደረገ በኋላ ህዝባችን ካለው ጨቋኝ ስርአት ኣገላግሎ በሀገራችን ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን እንዲሁም የህብረተሰባችን ኑሮ ከገባው የድህነት ወለል ለማውጣት በከፍተኛ ተግባራዊ ስራ ተጠምዶ ይገኛል።
  በዚ መሰረት ደግሞ የትህዴን ታጋዮች 16ኛው አመት የድርጅታችን ልደት በአል ሲያከብሩ በከፍተኛ ሞራልና የለውጥ መንፈስ ሁነው እንዳከበሯት ወኪሎቻችን ገለፁ።
   በበአሉ የተገኙት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በበኩላቸው የትህዴን ትግል ህዝባዊ ስለሆነ፣ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት እያገኘ እየመጣ ነው። እኛ በበኩላችን ትግሉን ለመደገፍ ከትናንትና በላይ ታጥቀን በትህዴን ጎን እንቆማለን፤ የሚቻለን እገዛ ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ገልጿል።


No comments:

Post a Comment