Saturday, March 4, 2017

የትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ለወራት ያህል በወታደራዊና ፖለቲካዊ ሲያሰለጥናቸው የቆየ ኣዳዲስ ምልምሎች የካቲት19 ቀን 2009 ዓ.ም ከፍተኛ የድርጅታችን ኃላፊዎችና ዕድሜ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርአት እንዳስመረቃቸው ወኪላችን የላከልን መረጃ ያመለክታል።



    የትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል የድርጅቱ ዋና እትብት በመሆን በርከት ላሉት አመታት ከተለያዩ የሃገራችን ቦታዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ለመጡ ወጣቶች እየተቀበለ በማሰልጠን የትህዴን ድርጅት በሰው ሃይሉ እንዲጎለብት እያደረገ የቆየ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ የህዝባቸው ጭቆና ለመፍታት ወደ ትህዴን ለተቀላቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ለወራት ያህል ፖለቲካዊና ወታሃደራዊ ሲያሰለጥናቸው ቆይቶ የካቲት19 ቀን 2009 ዓ.ም “ቅያ” በሚል ስያሜ በደማቅ ሁኔታ ኣስመረቃቸው።
   የ”ቅያ” ተመራቂዎች የምረቃ ግዜ በየካቲት 19 ቀን የድርጅታችን 16ኛው አመት የልደት በአል እየተከበረ በነበረ አጋጣሚ በመሆኑ የምርቃው ስነ-ስርአት በበለጠ ድምቀት እንደነበረውና የትህዴን የኪነት ቡዱን ደግሞ የተለያዩ የስነ ጥበብ ስራዋን በማቅረብ በአሉን በማድመቅ ላይ ትልቅ ሚና እንደተጫወተች በበአሉ የተገኙት የትህዴን ጋዜጠኞች ገለፁ።
   የትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ዋና ኣዛዥ ታጋይ ኃይላይ አባዲ በአሉን ኣስመልክቶ ባሰማው መግለጫ፦ የቅያ ተመራቂዎች በማሰልጠኛ ቤት እንዳሳሳያችሁት የምያስደንቅ እንቅስቃሴ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ በምትመደቡበት የትህዴን ክፍሎችና ሰራዊት እንደስማችሁ ቅያ፤ ታሪክ መስራት ኣለባችሁ ሲል መልእክቱን ኣስተላለፈ።
  በምርቃው ስነ-ስርአት የተገኘ የትዴን ሊቀ-መንበር ታጋይ መኮነን ተስፋይ ለድርጅታችን ትህዴን የልደት በአልና የምልምሎችን ምረቃ ኣስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ የመግለጫው ሙሉ ይዘትና ጠቅላላው የምረቃው ስነ-ስርአት በሚቀጥል የሮብ ስርጭታችን የምናቀርብ መሆናችንን መጠቆም እንፈልጋለን።

No comments:

Post a Comment