Thursday, March 16, 2017

በትግራይ ክልል መረብ ለኸ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች የስራ ዕድል ባለማግኘታቸው ባኣሁኑ ግዜ በብዛት ወደ ስደት እያመሩ እንደሚገኙ ታወቀ።



በማእከላዊ ዞን  መረብ ለኸ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች መንግስት ኣደራጅቶ የስራ ዕድል ሊከፍትላቸው ባለመቻሉ በአሁኑ ግዜ በርከት ያሉ ወጣቶች ኣከባቢያቸው እየለቀቁ ወደ ውጭ ሃገር እየጎረፉ እንደሚገኙ የኣከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
የወያኔ ስርዓት ስራ ለሌላቸው የትግራይ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመክፈት በሚል በሚሌዮኖች የሚቆጠር ብር በጀት ኣዘጋጅቻለሁ እያለ ባለበት በአሁኑ ግዜ ወደ ስደት የሚያመሩ የወረዳው ወጣቶች ብዛት እየጨመረ እንደሚገኝና፤ባህር ተሻግሮው ወደ ውጭ ሃገር ለመሄድ ሲሉ የተለያዩ ችግሮች እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይ ዜና በጨቃኙ የኢህአዴግ ስርዓት ኣገዛዝ ተማርሮው በርከት ያሉ የወረዳው ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ት.ህ.ዴ.ን) እየገቡ እንደሚገኙ ተደጋጋሚ ስንገልፅ መቆየታችን ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment