Thursday, March 16, 2017

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የምትገኝ ውቅሮ ከተማ በከተማዋ የቆሻሻ መጠራቀምያ ባለመኖሩ በፅዳት ላይ ትልቅ ችግር ፈጥሮ እንደሚገኝ የኣከባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች የቆሻሻ መጠራቀምያ እንዲመጣላቸው ለከተማዋ ኣስተዳደሪዎች በተደጋጋሚ ጠይቆው መልስ እንዳላገኙና የቖሻሻ መጠራቀሚያ ባለመኖሩ ሳብያ ቆሻሻው በከተሟ ውስጠ በየኣከባቢው ተጥሎ ስለሚገኝ ለኣከባቢው ህብረተሰብ  የጤና ቀውስ ሁኖ እንዳለ የከተሟ ነዋሪዎች እያማረሩ እንደሚገኙ ታውቋል።
የህወሃት ባለ-ስልጣናት የሃገርና ህዝብ ሃፍት እየዘመቱ በግል ጥቅማቸው ተሰማርተው ባሉበት በአሁኑ ግዜ የውቅሮ ከተማ ህዝብ በከተማቸው ያለ ችግር ለረዥም ግዜ ጠይቀው ሰሚ ኣካል እንዳላገኙ የገለጹ ሲሆን፤በተጨማሪ የህውሃት ኢህአዴግ ውቅሮ ከተማን በእድገቷና ጽዳቷ ዕድገት እንዳሳየች  እንደሚገልጿት ሳይሆን ከተሟ በድህነትና ኋላ ቀርነት መኖሯ ነዋሪዎቹ ጨምሮው  ኣስረድቷል።

No comments:

Post a Comment