Thursday, May 25, 2017

ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጭስ አባይ ከተማ ላይ የእጅ ቦንብ መወርወሩን ተከትሎ ባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ፌደራል ፖሊስ አባላት ተወረው እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል።



ለልማት በሚል በሚወሰድ መሬት የካሳ ክፍያ ውዝግብ መነሳቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ማንነታቸው ያልተወቁ ሃይሎች፣ በአካባቢው ነዋሪ የሆነና የህወሓት/ኢህአዴግ የመረጃ ሰው ነው በሚባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ቦንብ አፈንድተዋል።
ግለሰቡ በአካባቢው ያሉ አገዛዙን የሚቃወሙ አርሶአደሮችን እየጠቆመ እንደሚያሲዝ የተናገሩት ምንጮች፣ በተጣላው ቦንብም ልጁ ቆስሎ በህክምና ላይ ይገኛል። እንዲሁም ባህር ዳር ግንቦት 20 ቀበሌ ክልል ውስጥ ልዩ ስሙ ልደታ ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ አንድ ማንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ግለሰብ ሞቶ ተገኝቷል።



No comments:

Post a Comment