Sunday, June 11, 2017

የኢህአዴግ ስርዓት ሰራዊት ከሽሬ አካባቢ ወደ ጎንደር ከተማ እንደተንቀሳቀሰ ታወቀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት በርከት ያለ ቁጥር ያለው የገዢው ስርዓት ሰራዊት ግንቦት 28 2009 ዓ,ም ከሽሬ እንዳስላሴ አካባቢ ወደ ጎንደር ከተማ እንደተጓዘ ለማወቅ ተችሏል።
ባለፉት ግዜያት በደቡብ ጎንደር አድርጎ ወደ ሰሜን ጎንደር  ወገራ ወደ ተባለ ልዩ ቦታ እንደተሰባሰበ የገለፀው መረጃው፤ በተጨማሪም  የስርዓቱ ጦር ሰራዊት ተሰባስቦ ባለበት ቦታ የገበሬዎችን እንስሳት እና ንብረት እየዘረፈ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ቅጥረኛ የኢህአዴግ ሰራዊት ባለፉት ግዜያት በሰሜን ጎንደር  በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ  ሃይሎች ላይ ያደረገው ጥቃት ከመክሸፉ በኋላ፣ የገበሬዎችን እንስሳት ማለትም  ከብቶች ፤ፍየልእና በጎች በመዝረፍ አርዶ እየበላ እንዳለ ያአከባቢው ነባሪዎች ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት የስርዓቱ ሰራዊት በርከት ያሉ ያአከባቢው ቤቶችን እንዳቃጠለ እና በተጨማሪም፣ የአከባቢው ገበሬዎች በበርሃ አጭዶው የከመሩትን እና ያመረቱትን እህል፣ እንዳቃጠሉት ይታወቃል።
በመላ ሃገሪቷ በተለይም በባህርዳር እና ጎንደር ከተሞች እየተቀጣጠለ ያለዉ ህዝባዊ ተቃውሞ፣ እንቅልፍ ያሳጣው የኢህአዴግ ቡድን ተቃውሞውን በሃይል ለመጭፍለቅ ጦሩን በተለያዩ አቅጣጫዎች አድርጎ ወደ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በማዝመት ላይ እንደቆየ የተለያዩ ወገኖች ይገልፃሉ።


No comments:

Post a Comment