Saturday, June 3, 2017

በክልተ አውላዕሎ ወረዳ አይናለም ቀበሌ የእንስሳት ማቆሚያ የነበረውን ሰፊ የህዝብ መሬት፣ አንድ የወረዳው የም/ቤት አባል በፈላጭ ቆራጭነት ይዞ ለራሱ ጥቅም እንዳዋለው ታወቀ።



    በተገኘው መረጃ መሠረት፣ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፤ክልተ አውላዕሎ ወረዳ አይናለም ቀበሌ አንድ የወረዳው የም/ቤት አባል የቀበሌው ህዝብ  እንስሶቹን በጋራ ያሰማራበት የነበረውን ሰፊ መሬት ከህግ ውጪ ወሮ በመያዝ  ለግል ጥቅሙ አውሎት እንዳለ የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ይህ  ሰፊ የህዝብን መሬት በወረራ መልክ ይዞ ያለው ግለሰብ የወረዳው ም/ቤት አባል ስለሆነ፣ በህግ ፊት ቀርቦ ሊጠየቅ አልቻለም ያሉት ዜጎቹ፣ በተጨማሪም በወረዳው በርከት ያሉ የም/ቤት አባሎች የህዝብን መሬት ወርረው ይዘዉት እንዳሉ ያገኘነው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment