Saturday, June 3, 2017

በመረብ ለኸ ወረዳ ህገወጥ የመሬት ሽሚያና የደን ጭፍጨፋ በሰፊው እየታየ እንዳለ ተገለፀ።



   ከአከባቢው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው፣ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ወርዒ ለኸ ወረዳ አዝመራና ዓዲ አድሓ ቀበሌዎች፣የመሬት ሽሚያና ህገወጥ የደን ጭፍጨፋ በሰፊው የታየ እንዳለ የአከባቢው ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከአሁን በፊት በአንድ ላይ ትተዳደር የነበረች ሓዱሽ ዓዲ በመባል የምትጠራውን ጎጥ የወረዳው አስተዳዳሪዎች ከሁለት ከፍለው ወደ አዝመራና ዓዲ ሂደን ቀበሌዎች በመበተን፣ እንድትተዳደር ስለአድረጓት ለአከባቢው ነዋሪዎች በተለይም የሓድሽ ዓዲን ህዝብ አስቆጥቶ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
በወርዒ ለኸ ወረዳ ዓዲ ሂደንና አዝመራ ቀበሌዎች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ  ህገ ወጥ  የመሬት ሽሚያና የደን ጭፍጨፋ እንዳለ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
    በተጨማሪም የወረዳው አስተዳዳሪዎች ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ እየተነገራቸው  ጉዳዩን ሰምተው መልስ  እንደማይሰጡት ዜጎች ጨምረው አስረድተዋል።

No comments:

Post a Comment