Saturday, June 3, 2017

በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ማሕበራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አላረገልንም ሲሉ ወቅሰዋል።



   በጥቃቅን እና እነስተኛ ንግድ ተሰማርተው የሚሰሩ ዜጎች በመንግስት ድጋፍ ሊደረግላቸው ባለመቻሉ በስራቸው ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮባቸው እንዳለ አማረዋል።
በተለይ ደግሞ 147 ማሕበራት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት ችግራቸውን ቢገልፁም የሚያረካ መልስ አልተሰጠንም ሲሉ ተናግረዋል።
የማሕበሩ ወኪል አቶ የውሃንስ ገብሬ እንዳሉት ለግል ኩባንያዎች ሊሰጥ  የሚገባው ደረጃ ስድስት፣ ኮንትራክተር ማሟላት የሚገባቸውን ማስረጃ ሳያማሉ  ተሰጥቷቸው እያለ ፣ እኛ ግን በማሕበር ተደራጅተን እያለን በመንግስት እስከ  17 ሚልዮን ብር የሚገመት ስራ በተለያዩ የስራ መስክ መንግስታዊ ፕሮጀክት ሊሰጠን እየተገባ፣ ልናገኘው ባለመቻላችን የስራ እቃዎችን ለመግዛት ብድር  ለማግኘት አልቻልንም ሲሉ ገልፀዋል።
የማሕበሩ ተዋካዮች አጋጥሟቸው ላለው ችግር ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ አቤቱታ ቢያቀርቡም  ነገ ዛሬ እየተባሉ መቆየታቸውን ጠቅሰው፣ አሁን ደግሞ  ለቀጣይ ዓመት ጠብቁን የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment