Friday, March 16, 2018

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውጥረት በተሞላበት ሁኔታ መቀጠሉ ተሰማ።



   አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የመምረጡ ሂደት በፈጠረው ውዝግብ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰየሙ ሒደት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል። በሕወሃት ሰዎች እንዲሁም ከብአዴን አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው ከህወሃት ጎን በመሰለፍ ኦሕዴድን በማጥቃት ላይ መሆናቸውም ተመልክቷል።
  እሁድ የተጀመረውና የድርጅቱን ሊቀመንበር መምረጥን በዋናነት አጀንዳ ያደረገው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እንደተጠበቀው የድርጅቱን ሊቀመንበር ለፓርቲው ምክር ቤት ማቅረቡ አጠራጣሪ ሆኗል።  ዘግይተው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር የመምረጡ ሁኔታ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም በአቶ በረከት ስምኦን የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል።
  አቶ በረከት የሚያቀነቅኑት ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ጊዜ ይራዘም ሃሳብ በትንሹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስኪያበቃና እስከ ኢሕአዴግ ጉባኤ ድረስ እንዲቆይ መሆኑም ታውቋል። ሆኖም ስብሰባው አሁንም በዝግ በመቀጠሉ የትኛው ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ እንደሚወጣ እየተጠበቀ ይገኛል።

 

No comments:

Post a Comment