Monday, May 28, 2018

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ



በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡
ሊከሰት ለሚችለው የውኃ እጥረት መነሻው የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ የጀመራቸውን የውኃ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ የጠየቀው የውጭ ምንዛሪ ምላሽ ሳያገኝ አንድ ዓመት ሊያስቆጥር ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የከተማውን የውኃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት፣ በተለይ ሁለት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
እነዚህን ሁለት ፕሮጀክቶች ጨምሮ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለውኃ አቅርቦት ፕሮጀክቶች የጠየቀው፣ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ መሆኑ ታውቋል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ውኃው ወደ ሥርጭት ቢገባ የከተማው ውኃ አቅርቦት የመሻሻሉን ያህል ፕሮጀክቱ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ፣ በተለይ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የውኃ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል ጉዳዩን በቅርበት የማያውቁ የከተማው ባለሥልጠናት ከወዲሁ ሥጋት እንደገባቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment