www.demhit on line.com
በደረሰን
ዘገባ መሰረት መንግስት በሚያራምደው የከፋፍለህ ግዛፖሊሲ ምክንያት በአፋር ክልል ፤ ዞን 4 ፤ ወረዳ አውራ
ቦሂደሉና ኡሪኮማም ቀበሌዎች በሚገኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አንድ ሰው የሞተ ሲሆን ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ጉዳት ደርሶቦታል፣ ግጭቱን
ተከትሎ በአከባቢው ኗሪ የሆኑ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች በፖሊስ ተይዘው ፋንቲ ራሱ በተባለ ቦታ በሚገኝ አንድ እስር ቤት
ውስጥ ታስረው ሲሰቃዩ ከቆዩ ብሁዋላ በዋስ ተለቀዋል ፣መንግስት እየተከተለው ያለ ሃላፊነት የጎደለው አሰራር የህዝብን ቁጣ በመቀስቀሱ
በአሁኑ ግዜ በአከባቢው ውጥረት ሰፍኖ ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለጽ ላይ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
በቅርብ ግዜ በሞያሌ አከባቢ በሚገኙ
በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሞ ጎሳዎች መካከል እንዲሁም በፋርና በዒሳ ጎሳዎች መካከል ተመሳሳይ ግጭት መከሰቱ የሚታወስ ነው፣