Sunday, July 28, 2013

በኢህአዴግ ስርዓት ላይ እምነት ያጡት የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስርዓቱን በመካድ እግራቸው ወደ መራቸው በመጥፋት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ወደ ኤርትራ የገቡ አምስት ወታደሮች ገለጹ።



የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም ወደ ኤርትራ ከመጡት ወታደሮች መካከል፣-
1-ም/፶/አ ታደሰ አለባቸው ፤ ከሰሜን እዝ ፤ 14ኛ ክ/ጦር ፤ 2ኛ ሬጅመንት ፤ 4ኛ ሃይል አባል የነበረ ከብሄረ አማራ
2-ም/Þ/አ ተገኝ ክያ ፤ ከሰሜን እዝ ፤ 6ኛ ሬጅመንት ፤ 2ኛ ሃይል ፤ 3ኛ ጋንታ ፤ 3ኛ ቲም አባል የነበረ ከብሄረ ሲዳማ
3-ም/Þ/አ ደሴ ሞገስ ፤ ከሰሜን እዝ ፤ ከ 19ኛ ክ/ጦር ፤ 3ኛ ሬጅመንት ፤ 4ኛ ሃይል ፤ 1ኛ ጋንታ አባል የነበረ ከብሄረ ትግራይ
4-ወ/ር ሮሞዳን ጅኑብ ከሰሜን እዝ ፤ 4ኛ ክ/ጦር ፤ 6ኛ ሬጅመንት ፤ 4ኛ ሃይል ፤ 5ኛ ጋንታ አባል የነበረ ከብሄረ ኦሮሞ
5-ወ/ር ዓብዱረዛቕ መሓመድ ፤ ከሰሜን እዝ ፤ 21ኛ ክ/ጦር ፤ 4ኛ ሬጅመንት ፤ 3ኛ ሃይል ፤ 1ኛ ጋንታ አባል የነበረ ከብሄረ ኦሮሞ ሲሆን ሁሉም በስርዓቱ ላይ እምነት ማጣታቸውን ገልጸዋል። በተለይም ከ 19 ክ/ጦር የመጣው ወ/ር ደሴ ሞገስ ፤ ሰራዊቱ በአጠቃላይ በስርዓቱ ላይ እምነት እንደሌለውና በሰራዊቱ ውስጥም አንድነት እንደሌለ ጠቅሶ ወ/ሩ ከተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አለው እየተባለ የተለያዩ በደሎች ስለሚደርሱበት ስርዓቱን በመቃወም እግሩ ወደ መራው እየተሰደደ ነው ሲል አስተያየቱን ሰጥታል።