የሸራሮ ከተማን ለበርካታ አመታት ሲያስተዳድር የቆየው ጥላሁን በርሀ በከተማዋ ኗሪዎች ዘንድ ተቀባይነት
እንደሌለው የተገነዘበው ህወሓት ፥ ካድሬውን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የህዝቡን ስሜት ለመግዛት የተንቀሳቀሰ ቢሆኑም የከተማዋ ህዝብ
በኢህአዴግ ስርዓት ላይ የነበረውን እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ በአሁኑ ጊዜ በአንድ ድምጽ በመቆም የስርዓት ለውጥ
እንጂ የግለሰቦችን መቀያየር መፍትሄ አያመጣም በማለት ድርጊቱን አጣጥሎታል።
አስተዳደሩ ከፊታችን ገለል ማለቱ የሚጠላ ባይሆንም የግለሰቦችን መቀያየር የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል ብለን
ግን አናስብም ። ከተማዋን ሲያስተዳድር የነበረው ካድሬ የኢህአዴግ ስርዓት ውጤት ስለሆነ አሁን በከተማዋ እየታየ ላለው ዘርፈ ብዙ
ችግር ምንጭ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የፈጠረው ችግር ነው ብለን ነው የምንወስደው ። ካድሬው ሲከተለው የነበረ ብልሹ አሰራር
የገዥው ፓርቲ አሰራር ነጸብራቅ ነው በማለት በጸረ-ህዝቡ ስርዓት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል።