Wednesday, August 7, 2013

በአላማጣ ከተማ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢያችን ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር እንድንከፍል እየተገደድን ነው ይላሉ።




እንደ ከተማዋ ነጋዴዎች አባባል በከተማዋ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን በመክፈት እራሳቸውና ለመጥቀምና ለአከባቢው ህዝብም የስራ እድል በመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ወገኖች መንግስት ከገብያቸው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ ስላስገደዳቸው ለኪሳራ ተዳርገዋል።
ነጋዴዎቹ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ግብር ዳግም ታይቶ መሻሻል እንዲደረግበት ሃምሌ 21,2005 ዓ/ም ለሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ ቢያቀርቡም ፥ ሰሚ ስላላገኙ በከፍተኛ ወጪ ያቋቋሙትን ድርጅት በኪሳራ ለመዝጋት በመገደዳቸው በድርጅቱ ተቀጥረው ሲሰሩ የነብሩ የአከባቢው ኗሪዎችም ስራቸውን አጥተው በችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ።
የንግድ ድርጅታቸውን ከተዘጉባቸው የከተማዋ ነጋዴዎች መካከል፦
1-አቶ ሃይሉ ኮቤ-የሸቀጣ ሸቀጥ ድርጅት
2-አቶ ኑርሕሴን-የጨርቃ ጨርቅና ስፌት ድርጅት
3-ወ/ሮ ብርቱካን ጎይትኦም-የሆቴል አገልግሎት ይገኝባቸዋል።