የከተማዋ ኗሪ ህዝብን ሳያነጋግርና ቅድመ ዝግጅት ሳያደርግ መንግስት ድንገት ዶዘር አሰማርቶ በርካታ ቤቶችን
ያፈራረሰ ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ 200 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ኗሪዎች ቤት አልባ ሆነው ለዝናብ ፤ ለብርድና ጸሃይ
ተጋልጠው አውላላ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።
መንግስት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት በክረምት ወቅት ባልጠበቁት መንገድ ለብዙ ዓመታት የኖርበትን
መኖሪያ ቤታቸው ድንገት ፈርሶ ቤት አልባ የሆኑት ዜጎች ካሳና ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው የመንግስት አካል ጠይቀው
ምላሽ እንዳላገኙ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።