Monday, August 12, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ቤታቸው በጎርፍ የተዋጠው የከተማዋ ኗሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።




የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የጎርፍ ወሃን ማስወጫ ቦይ ስላልተሰራላቸው ሃምሌ 25,2005 ዓ/ም በጣለው ከባድ ዝናብ ከተማዋን ያጥለቀለቀ ሲሆን በተለይም የ 04 ና የ 03 ቀበሌ በጎርፍ በመዋጣቸው የአከባቢው ኗሪ ወደ ቤቱ ለመግባትም ሆነ ከቤቱ ለመውጣት አልቻለም ፣ ኗሪዎቹ በተኛው ውሃ ምክንያት ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ለተለያየ በሽታ በመጋለጣቸው ፤ በየወቅቱ ለከተማዋ መሰረተ ልማት የተዋጣው ገንዘብ የት ገባ ለደረሰው ችግር የከተማዋ መስተዳድር ተጠያቂ ነው የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማስተጋባት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
     ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በመሰብሰብ ምላሽ የሰጠው የከተማው የማዛጋጃ ቤት ሃላፊ ተኽላይ ገ/ሄር የተባለ ካድሬ ካሁን ቀደም ስለተዋጣው ገንዘብ በተመለከተ እኛን አትጠይቁን እንዲህ ያለ ድንገተኛ አደጋ ለማስወገድና እራሳችሁን ለበሽታ ላለመጋለጥ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አዋጡና ችግሩን ፍቱት ፥ ይህ ማድረግ ካልቻላችሁ መንደራችሁን አጥለቅልቆ በተኛው ውሃ ተጠቅማችሁ አሳ ብታረቡ ይሻላል ሲል በህዝቡ ችግር መሳለቁን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።