Tuesday, August 13, 2013

በአላጀ ወረዳ ለአረጋዊያንና በበሽታ ምክንያት ስራ ሰርተው እራሳቸውን መርዳት ለማይችሉ ወገኖች ተብሎ የተላከ እርድታ የወረዳዋ ባለስልጣናት ለግል ጥቅማቸው አዋሉት።




በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን እድሚያቸው ለገፉአረጋዊያንና በተለያየ በሽታ ምክንያት ሰርተው ኑራቸውን መምራት ለማይችሉ የህብረተሰቡ አባላት እንዲውል በሚል ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገኘ በ 10 ሽዎች ኩንታል የሚቆጠር እርዳታ የወረዳዋ የመስተዳድር አካላት ተረክበው ለችግረኞቹ ማከፋፈል ሲገባቸው በአቋራጭ ለመክበር በአከባቢው ለሚገኙ ‘ኡሁዳ’ ለተባለ የፈርኖ ዱቄት ፋብሪካ ሸጠው ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ቷውቋል።
በሌላ ዜና በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን የወልዲያ ከተማ የመስተዳድር አካላት በከተማዋ የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰቡ ክፍሎች ያለ ምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት መኖርያ ቤታቸውን በማፈራረስ ቦታው ለግል ባለ ሃብቶች እየተሸጠ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።