ሃምሌ 27,2005 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል በዋሪ ከተማ በተካሄደ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት በሃይማኖት
ውስጥ እጁን ማስገባት ያቁም? ድምጻችን ይሰማ? የኢህአዴግ ስርዓት በዜጎች ላይ እየፈጸመው ያለው እስራትና ግድያ እንዲያቆም ጠይቀዋል።
የከተማዋ የፖሊስ ሃይል ሰላማዊ ሰልፉን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም የህዝቡ ሃይል ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ
ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ሰላማዊ ሰልፉ ከተጠናቀቀ ብሁዋላ ለሊት 14 የፖሊስ አባላት የተገደሉ ሲሆን ከነዚሁ ውስጥ ስድስቱ የከተማዋ
የፖሊስ አባላት ሲሆኑ ስምንቱ ደግሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት ናቸው። በፖሊስ አባላቱ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን ድረስ ሃላፊነት
የወሰደ አካል የለም።