በዞኑ አስተዳደር የተመራና ሃምሌ 26,2005 ዓ/ም በተካሄደው ሰብሰባ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መንግስት ህገ-መንግስቱን እያከበረ አይደለም ፤ ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ
መሆናቸውን እየታወቀ የመንግስት ባለስልጣናት በሃይማኖት ውስጥ እጃቸውን ያስገባሉ ፣ የሃይማኖት ነፃነት የለም ፤ የሃይማኖት መሪዎቻችን
እራሳችን እንዳንመርጥ ታግደናል መንግስት ባስቀመጣቸው ሰዎች እየተመራን ነው ፤ መንግስት ከሃይማኖት እጁን ያንሳ በማለት በስርዓቱ
ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገጸዋል።
ተሰብሳቢዎቹ በማያያዝም መንግስት ጢሙን ላስረዘመ ‘ቢንላደን’ ፤ ስሪውን ላሳጠረ ‘አክራሪ’ ተሰባስበው
ለሚታዩ ጸረ-ህዝብና ሃገር በማለት ሙስሉሙን እያጥላላ ባለበት እንዴት መግባባት ይቻላል? ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ በአ/አበባ
ከተማ የሚገኘው አንዋር መስጊድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ መንግስትና የሙስሊሙን ህብረተሰብ የሚያቀራርብ አይደለም
የሚሉ ሃሳቦችን በማቅረባቸው ስብሰባው ያለውጤት መበተኑን ቷውቋል።