Saturday, September 21, 2013

የተለያየ ቃል ተገብቶላቸው በ 1990 ዓ/ም ወደ መከላከያ ሰራዊት እንዲገቡ የተደረጉና በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ከሰራዊቱ የተሰናበቱ ወታደሮች መብታችን ይጠበቅልን ሲሉ መንግስትን ጠየቁ።



በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወደ ውትድርና ዓለም እንዲገቡ የተደረጉና የተለያየ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው በህይወት የተረፉ ወታደሮች መብታቸው ስላልተከበረና ሰርተው ህይወታቸውን የሚመሩበትንም ሁኔታ ስላልተፈጠረላቸው እንደዚሁም በወቅቱ የተሰው ወታደሮች ቤተሰቦች የወራሽነት መብታቸው ስላልተከበረ ከሁሉም ክልሎች የድጋፍ ፌርማ በማሰባሰብ ከመሃከላቸው ሰዎችን በመምረጥ ፤ በመወከልና የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስፈልግ ገንዘብ በማዋጣት ወደ ሃገር መከላከያ ሚኒስትር መላካቸውን ቷውቋል።
ተወካዮቹ በከመከላከያ ሚኒስቴር በደረሱበት ወቅት ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር የገባችሁት ውል ስለሌለ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጥ ካሳም ሆነ የጡረታ መብት አይኖርም ነገር ግን በወቅቱ ለነብራችሁ ተሳትፎ ማመስገን እንወዳለን የሚል ነጭ ወረቀት ሰጥተው እንደሸኛቸው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።