በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ክልል ፤ አዊ ዞን ፤ ጃዊ ወረዳ የሚገኙ ገበሬዎች በኢህአዴግ ካድሬዎች
ተገደው እንዲወስዱት የተደረገ መዳበሪያ በጣም በመወደዱና ከመሬታቸው የአፈር ይዞታና የማዳበሪያ ዓይነትና አጠቃቀም ዙሪያ ዝርዝር
እውቀት በእርሻ ባለሞያዎች ስላልተሰጣቸው የዘሩት ሰብል ፍሪያማ ሊሆን ስላልቻለ በጭንቀት ላይ ይገኛሉ ።
የገበሬዎቹ ጭንቀት በእርሻው የሚፈለገውን ምርት ባለማግኘታቸው ብቻ ሳይሆን በብድር በውድ ዋጋ ተገደው እንዲወስዱት የተደረገውን ማዳበሪያ ዋጋ ቶሎ እንዲከፍሉ
በመንግስት ጫና እየተደረገባቸው በመሆኑም ጭምር ነው። ገበሬዎቹ የምርታቸውን ይዘት በማየት አስተያየት እንዲደረግላቸው መንግስትን
ጠይቀው የግድ የወሰዱትን ማዳበሪያ ዋጋ በተባለው ጊዜ መክፈል እንዳለባቸው በመመሪያ ጭምር ስለተነገራቸው በስርዓቱ ላይ እምነት
ማጣታቸውን ገልጸዋል።