በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ፤ የሰቲት ሑመራ ከተማ የመስተዳድር አካላት የከተማዋን የውስጥ ለውስጥ መንገድ
በአስፋልት ንጣፍ እንዲሰራ በሚል ሰበብ በያዝነው ሳምንት የከተማዋን ኗሪን በመሰብሰብ እያንዳንዱ ኗሪ ገንዘብ እንዲያዋጣ ቅስቀሳ
አካሂደዋል። ህዝቡ በከተማዋ መስተዳድር እምነት በማጣቱ ምክንያት የከተማዋን ልማት በማስመልከት በመስተዳድሩ እየተደረገ ያለውን
ቅስቀሳ በአንድ ድምጽ መቃወሙን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
መንግስት ነጋ ጠባ በሚያቀርበው የመዋጮ ብዛት በጣም የተሰላቹ የከተማዋ ናሪዎች ፥ የነበረን ሁሉ ጨርሰን
ከየት አምጥተን እንስጣችሁ በማለት በባለስልጣናቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በመግለጻቸው የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሬዎች በስብሰባው የተያዘውን
አጀንዳ በአግባቡ ሳይጠናቀቅ ለማቋረጥ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።